-->

Thursday, July 29, 2010

ለምን ጉዱ ካሣ

ጉዱ ካሣን የሚለው ስም እንግዳ አይደለም፡፡ ፍቅር አስከ መቃብር የተሰኘው ዝነኛ የአማርኛ ልብወለድ ገጸ ባሕርይ ስም ነው፡፡ ጉዱ ካሣን ከሌሎች ገጸ ባሕርይዎች ለየት የሚያደርገው ከወቅቱ የአስተሳሰብ እና ባሕል ወጣ ያሉ አስተያየቶች እና ራዕዮች የነበሩት ሰው በመሆኑ ነው፡፡ ሃሳቦች በወቅቱ ለነበረው ሕብረተሰብ በተለይ ለገዢው መደብ የማይዋጥ ቢሆንም ለምስኪኑ፤ የዚህን ዓለም ኑሮ ከታች ሆኖ ለሚመለከተው ለብዙኃኑ ግን ትርጉም የሚሰጥ ነበር፡፡ የፍቅር እስከመቃብሩ ጉዱ ካሣ በእና ዘመን ቢኖር ምን ያስብ እንደነበረ ሳስብ፤ እኔ ከማስበው ጋር ብዙ የሚስማማባቸው ነጥቦች እንዳሉ ስለገመትኩ ይህንን ድረ ገፅ ጉዱ ካሳ ላይቭ አልኩት፡፡ ጉዱ ካሣ በእኔ ውስጥ በሕይወት አለና፡፡

No comments:

Post a Comment